Fana: At a Speed of Life!

ቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ላኪዎች ተቀናጅተው መስራት ይገባቸዋል- ግብርና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቡና፣ ሻይ እና ቅመማ ቅመም ወደ ውጭ መላክ ላይ የተሰማሩ አካላት ተቀናጅተው መስራት እንደሚገባቸው የግብርና ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የ2015 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀምና የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የኢኮኖሚ አማካሪ አምባሳደር ግርማ ብሩ እና የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት እየተገመገመ ነው፡፡
በውይይቱ የቡና፣ ሻይ እና የቅመማ ቅመም ልማትና ግብይት የ2015 በጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድን የተመለከተ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
የቡናና ሻይ ባለስልጣን በተሰጠው ተልዕኮ መሠረት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እና ዘመናዊና ፍትሃዊ የግብይት ስርዓት ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑ በመድረኩ ተነስቷል፡፡
የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)፥ ወደ ውጭ የሚላኩ የግብርና ምርቶች ጥራታቸው የተጠበቁ እንዲሆን በዘርፉ የተሰማሩ ባለድርሻ አካላት ሁሉ በተቀናጀ እና በተናበበ መልኩ መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡
አምባሳደር ግርማ ብሩ በበኩላቸው÷ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮቹን ለመፍታት የችግሩን ዓይነት በመለየት መንግስት በትኩረት እንደሚሰራ መናገራቸውን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.