አቶ ሙስጠፌ ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ በዓለም የምግብ ፕሮግራም ከፍተኛ አማካሪ ማርክ ጎርዶን ከተመራ ልዑካን ቡድን ጋር ተወያዩ፡፡
ውይይቱ በክልሉ የምግብ እርዳታ አቅርቦት ፕሮጀክትን ለማሻሻልና መልሶ ለማስጀመር ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በውይይቱ ላይ የሥራ ሀላፊዎቹ በክልሉ የምግብ ድጋፉ የሚያስፈልጋቸው ወገኖች በአግባቡ ከምግብ ድጋፉ ተጠቃሚ በሚሆኑበትና በክልሉ እርዳታዎች በሚሰራጩባቸው አከባቢዎች ዙሪያ መምከራቸውን የክልሉ መገናኛ ብዙሐን ዘግቧል፡፡