Fana: At a Speed of Life!

በህገወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ የጦር መሳሪያ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በማዕከላዊ ጎንደር ዞን
ታች አርማጭሆ ወረዳ በህገወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ የጦር መሳሪያ ተያዘ።

ህገ ወጥ የጦር መሳሪያው መነሻውን ከምራብ ጎንደር ዞን ምድረ ገነት ከተማ አስተዳደር ወደ ጎንደር ከተማ ባደረገ የጭነት ተሽከርካሪ አይሱዙ ሻግ (እቃ መደበቂያ) ውስጥ ተደብቆ ወደ ጎንደር ለማለፍ ሲሞክር ነው የተያዘው።

በተደረገ ፍተሻ 37 ክላሽ፣ 9 ሺህ 277 የክላሽ ጥይቶች እንዲሁም 21 የክላሽ ካዝናዎች በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር በልዩ ኃይል አባላትና የመደበኛ ፖሊስ አባላት ትብብር ተይዟል።

የታች አርማጭሆ ወረዳ ሰላምና ደህንነት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አንተነህ ታደሰ እንደገለፁት፥ አሽከርካሪው እና አንድ ተጨማሪ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው።

ሃላፊው የጦር መሳሪያው ለህገ ወጥ ተግባርና ለአካባቢው ሰላም አደጋ ከመሆን ውጭ ጥቅም እንደሌለው በመረዳት በእንደዚህ አይነት ህገወጥ ተግባር የተሰለፉ እንዲታቀቡና ህብረተሰቡም ከጸጥታ ሃይሎች ጎን በመሰለፍ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ ማሳሳባቸውን ከታች አርማጭሆ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.