Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አመራሮች ጋር ተወያዩ

አበባ ፣ ሚያዚያ 30 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የበላይ ጠባቂ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የኮቪድ19 ወረርሽኝን በተመለከተ ከማህበሩ አመራሮች ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸውም ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ማህበሩ ወረርሽኙን በመከላከል ሂደት ውስጥ ያለውን ቁልፍ ሚና የበለጠ እንዲያጠናክር መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ኮቪድ19ን ለመከላከል በተለያዩ ከተሞች የኬሚካል ርጭት በማከናወን፣ በጎ ፈቃደኞችን በማሰማራት እና የንፅህና መጠበቂያዎችን በማሰራጨት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.