Fana: At a Speed of Life!

በግሪክ በተከሰተ ሰደድ እሳት የ18 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ምስራቅ ግሪክ ጫካ ውስጥ በተነሳ ሰደድ እሳት የ18 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡

በሰደድ እሳቱ ምክንያት ለህልፈት የተዳረጉ 18 ሰዎች አስከሬን በእሳት አደጋ መከላከል ሰራተኞች መገኘቱ ተመላክቷል፡፡

ሟቾቹ ከቱርክ ወደ ግሪክ የተሸጋገሩ ስደተኞች ሳይሆኑ እንዳልቀሩም አልጀዚራ በዘገባው አስፍሯል፡፡

ይህም በሀገሪቱ በተከሰተው ሰደድ እሳት በተያዘው ሳምንት ብቻ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎችን ቁጥር ወደ 20 ከፍ ያደርገዋል ተብሏል፡፡

የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር በመቶዎች የሚቆጠሩ የእሳት አደጋ መከላከል ሰራተኞች ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

የሰደድ እሳቱ አሁን ላይ በርካታ የሀገሪቱ አካባቢዎችን እያዳረሰ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.