Fana: At a Speed of Life!

“ብሪክስ” ይበልጥ እንዲጠናከር ሺ ጂንፒንግ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፍትኀዊ ዓለምአቀፋዊ ሥርዓትን ዕውን ለማድረግ የ”ብሪክስ አባል ሀገራት” ቁጥር መጨመር እና መጠናከር እንዳለበት የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንት ሺ በመልዕክታቸው ÷ ፍትኀዊ ዓለም አቀፋዊ ሥርዓትን ለመገንባት ቡድኑ ተጨማሪ በምጣኔ ሐብት በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን ቢቀበል መልካም መሆኑን አንስተዋል፡፡

“ቻይና ፍትኀዊ ዓለምአቀፋዊ ሥርዓት እንዲሰፍን እንጂ በበላይነት የመቆጣጠር ፍላጎት የላትም” ም ሲሉ ነው በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ እየተካሄደ በሚገኘው የአባል ሀገራቱ ስብሰባ ላይ በተወካያቸው በኩል መልዕክታቸውን ያስተላለፉት፡፡

በሀገሪቷ ንግድ ሚኒስትር ዋንግ ዌንታዖ በኩል ባስተላለፉት መልዕክት ቻይና ዓለምን የመቆጣጠርም ሆነ የኃይል ውድድር ውስጥ የመግባት ፍላጎት የላትም ብለዋል፡፡

ቻይና ፍትኀዊ በሆነ የጋራ ተጠቃሚነት እንደምታምንም ነው የገለጹት፡፡

ሺ በመልዕክታቸው ÷“ብሪክስ” ዓለምአቀፋዊ ተፅዕኖዎች ቢያይሉበትም እንኳ ማደጉን ይቀጥላል ማለታቸውንም አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.