አምባሳደር ሽፈራው (ዶ/ር) ከተመድ የኢትዮጵያ ተጠሪና የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተ/ማሪያም (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪና የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ራሚዝ አላክባሮቭ (ዶ/ር) ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይታቸውም በሰብዓዊ ድጋፎች ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው (ዶ/ር)÷ በኢትዮጵያ ስላለው የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ክፍተትና በኢትዮጵያ መንግስትና በተባበሩት መንግስታት ኤጀንሲዎች መካከል ስላለው ተቀራርቦ የመስራት ልምድን ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡
ራሚዝ አላክባሮቭ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው የስራ ቆይታ የነበረውን ተቀራርቦ የመስራት ልምድ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል፡፡
በተጨማሪም የሰብዓዊ ድጋፉን ክፍተት ለመሙላት በሚያስፈልገው ሁሉ ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ነው የገለጹት፡፡