Fana: At a Speed of Life!

መርማሪ ቦርዱ የጀመረውን ክትትልና ቁጥጥር እንዲያጠናክር ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ የጀመረውን ክትትልና ቁጥጥር አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ሎሚ በዶ አሳሰቡ፡፡

መርማሪ ቦርዱ እስካሁን ያከናወናቸውን ተግባራት ሪፖርት እና በቀጣይ የሚያከናውናቸውን ተግባራት ረቂቅ ዕቅድ ምክትል አፈ ጉባኤዋ እና የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚንስትር በተገኙበት አቅርቧል፡፡

ምክትል አፈ ጉባኤ ሎሚ በዶ መርማሪ ቦርዱ የተለያዩ ተጽዕኖዎች ሳይበግሩት ገለልተኛ ሆኖ እያከናወነ ስላለው ተግባር አመስግነው÷ በቀጣይም ክትትልና ቁጥጥሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡

በምክር ቤቱ የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚንስትር ተስፋዬ በልጅጌ÷ ቦርዱ ገለልተኛ ሆኖ ስራውን ያከናውን ዘንድ ምክር ቤቱ አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

መርማሪ ቦርዱ በቀጣይ የሚያከናውናችውን ተግባራት በሚመለከት የቀረበው ዝርዝር እቅድ እና የመተዳደሪያ ደንብ የተለያዩ የማስተካከያ አስተያየቶች ከቀረቡበት በኋላ መጽደቁን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.