Fana: At a Speed of Life!

የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጠናቀቃል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀንጋሪ ቡዳፔስት ለአንድ ሣምንት ሲካሄድ የቆየው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ምሽት በሚደረጉ ውድድሮች ፍፃሜውን ያገኛል፡፡

ምሽት 3፡10 ላይ በሚካሄደው የወንዶች 5 ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር÷ አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ፣ በሪሁ አረጋዊ እና ሐጎስ ገብረ ሕይወት ይጠበቃሉ፡፡

እንዲሁም ምሽት 4፡10 ላይ የሴቶች 3 ሺህ ሜትር የመሰናክል ፍጻሜ ውድድር የሚካሄድ ሲሆን÷ በዚሁ መርሐ ግብር አትሌት ሲምቦ ዓለማየሁ፣ ሎሚ ሙለታ እና ዘርፌ ወንድምአገኝ ተጠባቂ ናቸው፡፡

በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናው እስካሁን በተደረጉ ውድድሮቸ÷ ኢትዮጵያ በ9 ሜዳሊያዎች ከዓለም 5ኛ  እንዲሁም ከአፍሪካ ቀዳሚውን ደረጃ ይዛለች፡፡

አሜሪካ በ27 ሜዳሊያዎች በሻምፒዮናው የመጀመሪያውን ደረጃ ስትይዝ÷ ካናዳ፣ ስፔን እና ጃማይካ በቅደም ተከትል ከ1 እስከ 3 ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.