Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቅዱስ ጊዮርጊስ የዛንዚባሩን ኬ ኤም ኤም የእግርኳስ ቡድን በደርሶ መልስ በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል፡፡

ከሜዳው ውጭ 2 ለ1 አሸንፎ የተመለሰው ቅዱስ ጊዮርጊስ ÷ የመልሱን ጨዋታ 10 ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም አከናውኗል፡፡

በጨዋታው ፈረሰኞቹ ከመመራት ተነስተው በዳዊት ተፈራ፣ ናትናኤል ዘለቀ እና አማኑኤል አረቦ ጎሎች 3 ለ 1 ማሸነፍ ችለዋል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም ፈረሰኞቹ÷ 5 ለ 2 በሆነ ድምር ውጤት በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ችለዋል፡፡

በቀጣዩ ዙርም ከግብፁ አል አህሊ ጋር እንደሚጫወቱ የወጣው መርሐ ግብር ያስረዳል፡፡

ከቀናት በፊት በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ባህርዳር ከተማ የታንዛኒያውን አዛምን በመለያ ምት በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉ ይታወሳል፡፡

በሌላ በኩል በምስራቅ አፍሪካ የቻምፒየንስ ሊግ ማጣሪያ ውድድር የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች ቡድን የኬንያውን ቪጋ ኩዊንስ 2 ለ1 በማሸነፍ ለፍፃሜ አልፏል፡፡

የንግድ ባንክን ጎሎች ሎዛ አበራ እና አረጋሽ ካልሳ ናቸው ያስቆጠሩት፡፡

በፍጻሜው ጨዋታም ከታንዛኒያው ጄ ቲ ኬ ኩዊንስ ጋር ይገናኛሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.