የ953 ኪሎ ሜትር አዳዲስ መንገዶች ግንባታ ሥራ ተከናወነ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት ዓመቱ 953 ኪሎ ሜትር አዳዲስ መንገዶች ግንባታና 238 ኪሎ ሜትር የነባር መንገዶች የማጠናከር እና ደረጃ ማሻሻል ሥራ መከናወኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስታወቀ፡፡
አስተዳደሩ የሚያስተዳድረው የፌደራል መንገድ ሽፋን 30 ሺህ 549 ኪሎ ሜትር መድረሱ ተገልጿል፡፡
ከእዚህ ውስጥም 18 ሺህ 232 ኪሎሜትር አስፋልት እና 12 ሺህ 317 ኪሎ ሜትር ጠጠር መንገድ መሆኑን አስተዳደሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
27 የመንገድ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤቶች ተቋቁመው ድጋፍና ክትትል እያደረጉ እንደሚገኙም ተመላክቷል፡፡
254 ኪሎ ሜትር ከባድ ጥገና እና 11 ሺህ 685 ኪሜ ወቅታዊና መደበኛ ጥገና መከናወኑንም ነው አስተዳደሩ ያስታወቀው፡፡
በቀጣይም የመንገድ ጥገና ሥራውን ቀልጣፋ እና ተደራሽ ለማድረግ አስተዳደሩ በቅርቡ የተለያዩ የግንባታ ማሽነሪዎችን ግዢ በመፈጸም ለሁሉም የጥገና ዲስትሪክቶች ማሰራጨቱን ገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!