Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት ከስዊድኑ “ሚልዮማንኒግ” ጋር ውል አሠረች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በክኅሎት የዳበረ እና የሠለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት ስዊድን ሀገር ከሚገኘው “ሚልዮማንኒግ” ኩባንያ ጋር በትብብር መሥራት የሚያስችላትን የመግባቢያ ሥምምነት ተፈራረመች፡፡

የክኅሎት ሥልጠናው ኢትዮጵያውያን ሕጋዊ በሆነ የአሠራር ሥርዓት ስዊዲንን ጨምሮ ወደ ተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚያደርጉትን ጉዞ ከማሳለጥና አዳዲስ ክኅሎቶችን እንዲያገኙ ከማድረግ ባለፈ ለሀገር ውስጥ የሥራ ገበያም በማዘጋጀት ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ተብሏል፡፡

የሥራና ክኅሎት ሚኒስቴር ከሀገር ውስጥ ባለፈ የዓለምን የሥራ ገበያ ለመጠቀምና ፍልሰትን በአግባቡ ለማስተዳደር በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡

ሚኒስቴሩ ፍላጎቱ ያላቸውን ዜጎች በቂ ዕውቀትና ክኅሎት ይዘው እንዲሁም መብትና ደኅንነታቸው ተጠብቆ ወደ ተለያዩ የዓለም ሀገራት ሕጋዊ በሆነ መንገድ ተሰማርተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ በቴክኖሎጂ የታገዘ የአሠራር ሥርዓት ዘርግቻለሁ ብሏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.