Fana: At a Speed of Life!

በኤሌክትሮኒክ ንግድ ለሚሳተፉ ድርጅቶች ምቹ የስራ ከባቢ ለመፍጠር እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኤሌክትሮኒክ ንግድ ለሚሳተፉ ድርጅቶች ምቹ የስራ ከባቢን ለመፍጠር መንግስት በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በኤሌክትሮኒክ ንግድ ዘርፍ የሚያጋጥሙ ችግሮች እና ሊወሰዱ በሚገባቸው መፍትሄዎች ላይ ያተኮረ መድረክ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በመድረኩ የኤሌክትሮኒክ ንግድን ማዕከል ባደረገ ስራ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች መሳተፋቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

በዘርፉ እያጋጣሟቸው ያሉ መሰናክሎችና ሊወሰዱ ስለሚገባቸው መፍትሄም አንስተዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ የኤሌክትሮኒክ ንግድን ለማሳለጥ የግሉ ዘርፍ ዋና ባለቤት ነው ብለዋል፡፡

መንግስት፣ የግሉ ዘርፍ እና የሲቪል ማህበረሰቡ በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል፡፡

በኢትዮጵያ የኤሌክትሮኒክ ንግድ የተሳለጠ እንዲሆን የሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት በጋራ መስራት እንዳለባቸው እና በኤሌክትሮኒክ ትራንዛክሽ አዋጅ ላይ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚገባ ተሳታፊዎች አንስተዋል።

የመረጃ ልውውጥ እና የገንዘብ ዝውውር በኤሌክትሮኒክ መልክ ሲፈፀም ህጋዊ ማዕቀፍ እንዲኖረው የሚያስችል የኤሌክትሮኒክ ትራንዛክሽን ህግ ፀድቆ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.