ከሐሰተኛና ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ቢራ ሰፈር በግለሰብ መኖሪያ ቤት 200 ሺህ ሐሰተኛ ብር እና 700 የአሜሪካ ዶላር ተይዟል፡፡
ከዚሁ ወንጀል ጋር በተያያዘም ሁለት ተጣርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው እየተጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡
በዓላት ሲቃረቡ ሐሰተኛ ብርን ወደ ሕብረተሰቡ ለማሰራጨት እንቅስቃሴ እንደሚደረግ ያስታወሰው ፖሊስ፥ ሕብረተሰቡ በግብይት ወቅት ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል፡፡
አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙም ለፀጥታ አካላት ጥቆማ መስጠት እንደሚያስፈልግ ነው ያስገነዘበው፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!