መንግስት በሀገሪቱ የህግ ማዕቀፎች ተመስርቶ ከረድዔት ድርጅቶች ጋር ይሠራል – አምባሳደር ሽፈራው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተ/ማርያም (ዶ/ር) መንግስት ሁሌም በሀገሪቱ የህግ ማዕቀፎች ላይ ተመስርቶ ከአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤይድ) ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ገለጹ፡፡
የኮሚሽኑ አመራሮች አዲስ ከተመደቡት የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት በኢትዮጵያ ዳይሬክተር እስኮት ሆክለንደር ፣ ምክትሎቻቸው እና የድርጅቱ የሰብዓዊ ድጋፍ ጽሕፈት ቤት ዳይሬክተር ዴኒስ እስቶራ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትና እያጋጠሙ ባሉ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው (ዶ/ር) መንግስት ሁሌም በተለመደውና በሀገሪቱ የፖሊሲና የህግ ማዕቀፎች ላይ ተመስርቶ ከዩ ኤስ ኤይድ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠውላቸዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!