Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪደር የኮሮና ቫይረስ ሊያስከትል የሚችለውን ጫና መቀነስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ከኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪደር የጋራ ኮሚቴ ጋር ተወያይተዋል።

በዚህም በኢትዮ-ጅብቲ ኮሪደር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሊያስከትል የሚችለውን ጫና ለመቀነስና ሎጂስትክሱን ለማሳለጥ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።

ሚኒስትሯ የተጀመረው ቅንጅታዊ አሰራር ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ በመግለፅ በሎጅስቲክስ ዘርፉ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በመከላከል አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል የሚደረገው እንቅሰቃሴ የሚበረታታ መሆኑን መግለፃቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.