የናይጄሪያ ባለሐብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ-ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ሥምምነት ላይ ተደረሰ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የናይጄሪያ ባለሐብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ-ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ሥምምነት ላይ ተደረሰ፡፡
ባለሐብቶቹ በኢትዮጵያ ከሚገኙ አቻ ተቋማትና ባለሐብቶች ጋር ተገናኝተው እንዲሠሩ ሁኔታዎች እንደሚመቻችላቸው መገለጹን በሌጎስ በተካሄደው ዓለምአቀፍ የንግድ ጉባዔ ላይ የተሳተፈው አቡጃ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡
ኤምባሲው በንግድ ጉባኤ ተሳትፎው ለኢትዮጵያ የወጪ ምርቶች ገበያ ማፈላለግ የሚያስችል ሁኔታ ማመቻቸቱን ጠቁሟል፡፡