Fana: At a Speed of Life!

በሰመራ ከተማ የተገነባው ኢፋ ቦሩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ድጋፍ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ የተገነባው ኢፋ ቦሩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመርቋል፡፡

በምረቃ መርሐ ግብሩ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እና ሌሎች የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ትምህርት ቤቱ ደረጃቸውን የጠበቁ የመማሪያ፣ የቤተ ሙከራ፣ የቤተ መጻሕፍት፣ የአስተዳደርና ሌሎች አገልግሎት መስጫ ክፍሎችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

ትምህርት ቤቱ ከ2 ሺህ በላይ ተማሪዎችን የመቀበል አቅም እንዳለው ተመላክቷል።

አቶ ሽመልስ ÷ የተገነባው ትምህርት ቤት የኦሮሞ ሕዝብ ለአፋር ሕዝብ ያበረከተው የወንድማማችነት ስጦታ ነው ብለዋል፡፡

ኩሩና የረጅም ታሪክ ባለቤት በሆነው በአፋር ሕዝብ መካከልና የመላው ሰው ልጅ የህልውና ምልክት በሆነው በአፋር ምድር በመገኘታቸው መደሰታቸውንም አንስተዋል፡፡

“ካለን ላይ በመቀነስ በሰመራ ከተማ ለአፋር ልጆች የገነባነው ት/ቤት መጪውን ትውልድ በእውቀት ለማብቃት ያለንን ቁርጠኝነት ማሳያና መታሰቢያ ሀውልት ሆኖ የሚቆም ነው”ሲሉም ገልጸዋል።

“ያለንበት ዘመን የውድድር ዘመን ብቻ ሳይሆን የመደጋገፍና የመተባበር ዘመን መሆኑን ተረድተን ለሀገራችን ህዝቦች የጋራ ለውጥና ብልፅግና የድርሻችንን እየተወጣን እንገኛለን” ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.