“ግጭት ውስጥ የገቡት ኤርትራውያኑ ሥደተኞች ከእስራዔል በአስቸኳይ እንዲወጡ እፈልጋለሁ” – ቤኒያሚን ኔታንያሁ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቴል አቪቭ ከተማ በተከሰተው ግጭት የተሳተፉ ኤርትራውያኑ ሥደተኞች በአስቸኳይ እስራዔልን ለቀው እንዲወጡ እንደሚፈልጉ የእስራዔል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ገለጹ፡፡
ኔታንያሁ ጉዳዩን አስመልክተው በሠጡት አስተያየት÷ በጥገኝነት እስራዔል የሚገኙ አፍሪካውያን ሥደተኞች በሙሉ በአስቸኳይ ሀገሪቷን ለቀው እንዲወጡም እንዲታሰብበት ማሳሰባቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት ይኅን ያሉት ÷ በትናንትናው ዕለት የኤርትራ ተቀናቃኞች ከእስራዔል ፖሊስ ጋር ደም አፋሳሽ ግጭት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ ነው፡፡
በደቡብ ቴል አቪቭ በተቀሰቀሰው ግጭት ከደርዘን በላይ ሰዎች መቁሰላቸው በዘገባው ተመላክቷል፡፡
በእስራዔል የሚገኙት የኤርትራ ሥደተኞች በቀሰቀሱት ግጭት የግንባታ እንጨቶችን፣ የብረት ቁርጥራጮችን እና ድንጋዮችን ተጠቅመዋል ተብሏል፡፡
የሱቅ መስኮቶችን እና የፖሊስ መኪናዎችን መሰባበራቸውም ነው ተነገረው፡፡
የእስራዔል ፖሊሶች የተለያየ ዓይነት አድማ በታኝ ጭስ እና አስደንጋጭ የእጅ ቦምቦችን በመጠቀም ሁኔታውን በቁጥጥር ሥር ለማዋል መሞከራቸው ተገልጿል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!