Fana: At a Speed of Life!

የአገልጋይነት ቀንን ምክንያት በማድረግ ነጻ የጤና ምርመራ አገልግሎት እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር ጳጉሜን 1 የአገልጋይነት ቀንን ምክንያት በማድረግ ነጻ የጤና ምርመራ አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ አስጀምሯል፡፡

በመርሐ ግብሩ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምጸሃይ ጳውሎስ፣ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እና የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ ( ዶ/ር) ተገኝተዋል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ÷ አገልጋይነት ሌላውን እንደ ራስ አድርጎ ማየትን የሚጠይቅ ተግባር መሆኑን አውስተዋል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲሠጥ በነበረው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አመርቂ ውጤት መመዝገቡንም ገልጸዋል፡፡

በዚህም እስካሁን ከ1 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ ዜጎች ልዩ ልዩ የጤና ምርመራና ሕክምና አገልግሎቶች በነጻ በማግኘት ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በአገልጋይነት ቀንም በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀምበር ለ250 ሺህ በላይ ዜጎች የነጻ ጤና ምርመራና ሕክምና አገልግሎት ለመስጠት መታቀዱን አስታውቀዋል፡፡

ወ/ሮ ዓለምጸሃይ ጳውሎስ በበኩላቸው÷ ሀገር የምታድገው በቅንነትና በታታሪነት በሚያገለግሉ ዜጎቿ መሆኑን ጠቁመው÷ ሁሉም አገልጋይ ለበለጠ ትጋት ሊነሳሳ ይገባል ማለታቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.