አይነ ስውር ተማሪዎች ትምህርታቸውን በተሻለ ሁኔታ መከታተል እንዲችሉ የሚያግዝ የድጋፍ ስምምነት ተፈረመ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 5 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አይነ ስውር ተማሪዎች ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ትምህርታቸውን በተሻለ ሁኔታ መከታተል እንዲችሉ የሚያግዝ የድጋፍ ስምምነት ተፈረመ።
የድጋፍ ስምምነቱ በተስማሚ ቴክኖሎጂ ማዕከል ለአይነ ስውራን እና በትምህርት ሚኒስቴር መካከል ተፈርሟል።
ስምምነቱ አይነ ስውራን ተማሪዎች በኮምፒዩተር፣ በብሬልና በአጋዥ መሳሪያዎች ታግዘው ትምህርታቸውን መከታተል እንዲችሉ የሚያደርግ በመሆኑ በተማሪዎቹ የመማር ሁኔታ ላይ ሊፈጥር የሚችለው አዎንታዊ ተጽዕኖ ከፍተኛ ይሆናል ተብሏል።
የተስማሚ ቴክኖሎጂ ማዕከል ለአይነ ስውራን እና ትምህርት ሚኒስቴር ለወደፊቱ በጋራ በመስራት ልዩ እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች እገዛ እንደሚያደርጉ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።