ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በልማት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን ለመገምገም ጅማ ገቡ
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 18 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በልማት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን ለመገምገም ጅማ ገብተዋል።
ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና የፌዴራልና የክልል አመራሮች አብረው መግባታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።