Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ ማዕከላት የሚገኙ ሠልጣኞች የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ “ዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሐሳብ በደሴ፣ ባሕር ዳር፣ ሐዋሳ፣ ሆሳዕና እና ሚዛን አማን ማዕከላት እየተሰጠ በሚገኘው 2ኛው ዙር ሀገር አቀፍ ስልጠና እየተሳተፉ የሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች የልማት ሥራዎችን ጎበኙ፡፡

በደሴ ማዕከል ስልጠናቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ አመራሮች÷ በደቡብ ወሎ ዞን ሀርቡ ከተማ የሚገኘውን የቃሉ ወረዳ የቆላ ፍራፍሬ የችግኝ ጣቢያ ጎብኝተዋል፡፡

በቀጣይም በደሴ እና ኮምቦልቻ አካባቢዎች የሚገኙ የልማት ሥራዎችን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል ተብሏል፡፡

በተመሳሳይ በባሕር ዳር ማዕከል ያሉ ሰልጣኞች÷ በባሕር ዳር ከተማ የሚገኙ ትላልቅ ኢንዱስትሪዎችን፣ የዓባይ ድልድይ፣ ዓባይ የምግብ ዘይት ፋብሪካና የአረንጓዴ ልማት ሥፍራዎችን ጎብኝተዋል።

እንዲሁም በሐዋሳ ማዕከል ስልጠናቸውን የሚከታተሉ አመራሮች÷ በክልሉ የተሠሩ የግብርና ልማት ሥራዎችን፣ የኢንዱስትሪ ልማት እና የሌማት ትሩፋት ተግባራትን በአራት ክላስተር ተከፋፍለው መጎብኘታቸው ተገልጿል፡፡

የሆሳዕና ማዕከል ሰልጣኞችም÷ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በገጠርና በከተማ የተከናወኑ የተመረጡ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል መባሉን ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በሚዛን አማን የስልጠና ማዕከል እየሰለጠኑ የሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች÷ የበበቃ ኮፊ እስቴት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ የቡና ልማት፣ የቁንዶ በርበሬ ልማት፣ በኩታ ገጠም እየለማ ያለ ማንጎና ሙዝ እንዲሁም የገበታ ለትውልድ አካል የሆነው የደንቢ ሰው ሰራሽ ሐይቅና ፏፏቴን መጎብኘታቸው ተመላክቷል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.