Fana: At a Speed of Life!

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የተሰራ “ሥውር ውጊያ” የተሰኘ ፊልም ምርቃት ስነ -ስርዓት ተካሄደ

 

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 4 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የተሰራ ‘”ሥውር ውጊያ” የተሰኘ ፊልም ምርቃት ስነ -ስርዓት ተካሄደ፡፡

ፊልሙ በሳይበር አለም የሚያጋጥሙ እውነተኛ ሁነቶች ላይ ተመስርቶ የተሰራ እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የስራ እንቅስቃሴዎችን የሚያሳይ ነው ተብሏል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሳይበሩን አለም ውጊያ ለመመከት እየሰራ ያለውን፣ የደረሰበትን አቅምና የቀጣይ ዝግጅቱን የሚያሳይ ጭብጥ እንዳለውም ተገልጿል።

በምርቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና ተማሪዎች ተገኝተዋል።

የፊልሙ ደራሲ ቻላቸው ፈረጀ ፣ በዝግጅት ምስጋና አጥናፉ የተሳተፉበት ሲሆን÷ በትወና አንጋፋና ወጣት ተዋንያን ተሳትፈውበታል።

“አይበገሬ የሳይበር አቅም ለሃገር ሉዓላዊነት” በሚል መሪ ቃል የጥቅምት ወር ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር በሚል የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሮች በመካሄድ ላይ እንደሆነ ይታወቃል።

በዛሬው መርሃ ግብርም ወሩ በርካታ ስራዎች የሚከናወንበት እንደሆነ ተመልክቷል።

በመድረኩ “ሥውር ውጊያ” ፊልም ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ታላቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦች እና ተቋማት የእውቅና እና ምስጋና ሽልማት መርሀ ግብር ተከናውኗል፡፡

 

በፍሬሕይወት ሰፊው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.