የሰንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 16ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በተለያዩ መርሐ ግብሮች በመላ ሀገሪቱ ተከበረ፡፡
ቀኑ “የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችንና ለሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የተከበረው፡፡
ሀገራዊ ወቅታዊ ሁኔታን በዋጀ መልኩ ከሰንደቅ ዓላማ መርሆች ጋር ተገናዝቦና ሀገራዊ ሪፎርሙን በሚያስቀጥሉ ውይይቶች ታጅቦ በመላ ሀገሪቷ መከበሩ ተጠቁሟል፡፡
በዓሉ በፌዴራል የመንግስት ተቋማት፣ በክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች፣ በመከላከያ ሠራዊት ካምፖች እንዲሁም በኤምባሲዎች እና የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች በደማቅ ሁኔታ መከበሩ ተገልጿል፡፡