Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ካለፈው ዓመት የተሻለ ውጤት ተመዝግቧል – የክልሉ የትምህርት ቢሮ

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በተለያዩ ችግር ውስጥም ሆኖ በ2015 ዓ.ም የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የተሻለ ውጤት ካለፈው ዓመት አንጻር የተሻለ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን የክልሉ የትምህርት ቢሮ ገለፀ፡፡

በክልሉ የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና አሰጣጥና ውጤትን በተመለከተ መግለጫ የሰጡት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ሃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) እንዳሉት÷ በ2015 የ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ለመፈተን ከተመዘገቡ 214 ሺህ 997 ተማሪዎች ውስጥ 210 ሺህ 323 ተማሪዎች ተፈትነዋል።

በክልሉ የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት በተፈጥሮ ሳይንስ 646 ሲሆን ÷ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 533 ነው ብለዋል።

አጠቃላይ በክልሉ 60 ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸውን ገልፀው፤ በ2015 የትምህርት ዘመን ፈተና ውጤት ከ2014 ዓ.ም ጋር ሲነፃፀርም የ0 ነጥብ 4 በመቶ እድገት አሳይቷልም ተብሏል።

በክልሉ የ12ተኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑ 574 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 77 ትምህርት ቤቶች ከ50 በመቶ በታች ውጤት ተመዝግቦባቸዋልም ነው ያሉት።

ይህም በክልሉ የታዩ የተለያዩ ችግሮች ተደምረው ያስከተሉት ውጤት መሆኑን ያነሱት የትምህርት ቢሮ ሃላፊዋ ሆኖም የተመዘገበው ውጤት ክልሉ በሀገር አቀፍ በአራተኛ ደረጃ እንዲቀመጥ አስችሏል ብለዋል።

በቀጣይ የተሻለ ውጤት በክልሉ እንዲመጣ ህብረተሰቡ የክልሉን ሰላም ለማስፈን በጋራ እንዲሰራ ጥሪ ቀርቧል።

በታሪኩ ለገሰ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.