ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በ3ኛው የቤልት ኤንድ ሮድ ፎረም ላይ ንግግር አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ3ኛው የቤልት ኤንድ ሮድ ፎረም መክፈቻ መርሐ- ግብር ላይ ንግግር አድርገዋል፡፡
በንግግራቸውም÷ የቻይና-አፍሪካን ግንኙነት ጥንተ መሰረት እና እድገት አውስተዋል፡፡
በቤልት ኤንድ ሮድ ፎረም የመሰረተ ልማት ክንውን በአፍሪካ አህጉር የተጣለውን ጠንካራ የትብብር መሰረትም አንስተዋል::
በማደግ ላይ ያለውን የአፍሪካን ተፅእኖ የመፍጠር አቅም አፅንዖት የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)÷ በባለብዙ ወገን መድረኮች አካታችነትን ማረጋገጥ ተገቢ መሆኑን አስረድተዋል::