ከ155 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን 155 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የሚገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን አስታወቀ፡፡
ከዚህ ውስጥ 131 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች ሲሆኑ 23 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር የሚገመቱት የወጭ የኮንትሮባንድ እቃዎች ናቸው፡፡
ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት፣ ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ የምግብ ዘይትና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡
የኮንትሮባንድ እቃዎቹ ከመስከረም 26 እስከ ጥቅምት 1 ቀን 2016 ዓ.ም ኮሚሽኑ ባደረገው ክትትል መያዛቸው ተገልጿል።
በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የገቢ እና የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር አዋሽ፣ ድሬዳዋ እና ሞያሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ መባሉን ከጉምሩክ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡