ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቻይና ጉብኝታቸውን አጠናቀው አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 10 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቻይና ያደረጉትን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አጠናቀው ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቻይና ቆይታቸው በ3ኛው የቤልት ኤንድ ሮድ ጉባኤ ላይ ተሳትፈዋል።
እንዲሁም ከፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ከየልዑካን ቡድናቸው ጋር በመሆን በቻይና ታላቁ የህዝብ አዳራሽ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
በተጨማሪም በቤልት ኤንድ ሮድ ጉባኤ የጎንዮሽ መድረክ ከኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ ፕሬዚዳንት ዲልማ ሩሴፍ ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውም ይታወሳል።
ከጉባኤው እና ውይይታቸው ባለፈም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሻንጋይ የያንግሻን ወደብ፣ ሻንጋይ ስቶክ ገበያ እና ሁዋዌ ማዕከልን ጎብኝተዋል።
ከሻንጋይ ጉብኝታቸው በኋላም በቻይና ሲዥዋን ግዛት የምትገኘውን አረጓንዴዋን የቼንግዱ ከተማን ጎብኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቻይና ያደረጉትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት እና በቤልት ኤንድ ሮድ ጉባኤ ላይ የነበራቸውን ተሳትፎ በማጠናቀቅም ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ መግባታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።