ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎችና የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች በባህር ዳር ከተማ ጉብኝት አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎችና የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች በባህር ዳር ከተማ እየተገነቡ የሚገኙ መሰረተ-ልማቶችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ዳይሬክተር ጀነራል ተመስገን ጥሩነህ፣ የጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል።
አመራሮቹ በባህር ዳር ከተማ እየተገነባ ያለውን የዓባይ ተለዋጭ ድልድይ ግንባታ ያለበትን ደረጃ መመልከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በተጨማሪም የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም በአመራሮቹ የተጎበኘ ሲሆን ፥ በቀጣይ ስታዲየሙን ለማጠናቀቅ በሚደረገው ጥረት ድጋፍ እንደሚደረግም ነው የተገለጸው።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!