Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል የበጋ መስኖ ልማት ንቅናቄ መድረክ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ የ2016 ዓ.ም የበጋ መስኖ ልማት ንቅናቄ መድረክ አካሂዷል፡፡

በመርሐ ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ የሥራ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ መምሩ ሞኬ÷ የመስኖ ልማት ንቅናቄን በሚመለከት ባቀረቡ ሰነድ ላይ ውይይት መካሄዱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

የሲዳማ ክልል በዘንድሮ በጋ ከአምናው የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ከአሁኑ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነ ሲሆን በዘንድሮ በጋ ከ68 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ለማልማት እየሠራ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.