Fana: At a Speed of Life!

የምስጋናና የሰላም ኮንፍረስ በአዲስ አበባ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች “ቀጣይ ምዕራፍ ለሁለተናዊ ለውጥ” በሚል መሪ ሃሳብ ያዘጋጀው የምስጋናና የሰላም ኮንፍረስ በሚሊኒየም አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋን ጨምሮ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ሌሎች የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ የሙስሊሙ ኡማ ከ1960 ጀምሮ ሰላማዊ ጥያቄዎችን ሲጠይቅ እንደነበር ተገልጿል፡፡

በዚህም ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት እንደተፈቀደ እና ሙስሊሙ ሰብሰብ ብሎ ለኢድ ሰላት መስገጃ ቦታ ይሰጠን በሚል ለጠየቁት ጥያቄ ምላሽ እንዳገኘ በመርሐ ግብሩ ተገልጿል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና መንግስታቸው የገቡትን ቃል ስለጠበቁ ምስጋና ይገባቸዋልም ተብሏል።

በመርሐ ግብሩ አምባሳደሮች፣ ዳያስፖራዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም ተገኝተዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፥ ለውጡን ተከትሎ ብዝሃነትን ታሳቢ በማድረግ በእኩልነት ለተሰጠው አገልግሎትና ለመጣው ፍትሃዊነት በህዝበ ሙስሊሙ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ለከተማ አስተዳደሩና ለእኔ ለሰጡኝ እውቅና ከልብ ላመሰግን እወዳለሁ ብለዋል፡፡

በቀጣይም ለህዝቦች እኩልነት፣ ለሰላም እና አብሮነትን ለማረጋገጥ፣ ፍትሃዊ አገልግሎት በመስጠት በከተማችን ከሚገኙ ከተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት ጋር በቅርበት መስራታችንን እንቀጥላለንም ነው ያሉት።

በፈትያ አብደላ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.