Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የአመራሮች የግምገማ መድረክ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በየደረጃው ያሉ የሥራ ሀላፊዎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የግምገማ መድረክ በቦንጋ ከተማ መካሄድ ጀመረ፡፡

በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር)÷ መድረኩ ወቅታዊ ክልላዊ የፖለቲካ ጉዳዮችን በመገምገም በየደረጃው በሚናከናወኑ ተግባራት ላይ የፖለቲካ አስተሳሰብና የተግባር አንድነት ለመፍጠር ታልሞ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

ህዝቡ በሚፈልገው ልክ ምላሽ ለመስጠት ከክልል ጀምሮ በየደረጃው ያለው መዋቅር ድረስ በአመራሮች ዘንድ የአስተሳሰብ፣ አመለካከት እንዲሁም በተግባር አፈጻጸም ላይ የሚታየውን ጉድለት በየጊዜው በመገምገም ችግሮችን መፍታት እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል፡፡

የግምገማ መድረኩ እስከታችው መዋቅር ድረስ እንደሚቀጥልም መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማሞ በበኩላቸው÷ አመራሩ የሚታይበትን የአመለካከት ችግር ማስተካከል እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡

መድረኩ እስከ አራት ቀናት እንደሚቆይም ተገልጿል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.