የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 18ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በኦሮሚያ ክልል ደረጃ በማያ ከተማ እየተከበረ ነው።
በበዓሉ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሰዓዳ አብዱረህማንና ሌሎች የሥራ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
ወ/ሮ ሰዓዳ አብዱረህማን በወቅቱ÷ በዓሉ ለህዝቦች እኩልነት መከበር የተከፈለውን ዋጋ የምንዘክርበት ነው ብለዋል።
በኦሮሚያና ከኦሮሚያ ክልል ውጪ ከሚገኙ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን የምናጠናክርበት ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በፌዴሬሽን ምክር ቤት የአስተዳደር ወሰንና ሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ ፀሐፊ አቶ ፍቅሬ አማን÷ ኢትዮጵያ ያላትን ብዝሃነት ለአንድነት መጠቀም ያሻል ብለዋል።
ለዚህም ያስችል ዘንድ የዘንድሮው በዓል ከሚከበርበት ዕለት አስቀድሞ በተለያዩ ስያሜዎች እንዲከበር መደረጉን ነው የገለጹት፡፡
የማያ ከተማ ከንቲባ ኢፍራ ወዚር (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ በዓሉ የማያ ከተማ በተመሠረተች ማግስት መከበሩ ለየት ያደርገዋል ብለዋል።