Fana: At a Speed of Life!

የቻይና ማሽነሪ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካ የመገንባት ፍላጎት እንዳለው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና ማሽነሪ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካ የመገንባት ፍላጎት እንዳለው ተገለጸ።

በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው የኮርፖሬሽኑን የስራ ሃላፊዎች ዛሬ በሚሲዮኑ ተቀብለው ውይይት አድረገዋል፡፡

በውይይቱም ኮርፖሬሽኑ በኢትዮጵያ የፖታሽ ማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ፍላጎት ያለው መሆኑ ተገልጿል።

በኢትዮጵያ በዘርፉ ትልቅ አቅም ያለውና በግብርናው ዘርፍ ያለውን የማዳበሪያ እጥረት የሚቀርፍ መሆኑ ተነግሯል።

የኮርፖሬሽኑ ስራ መጀመር የግብርና ዘርፍ ማነቆዎችን ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት ከማገዙም በላይ በምግብ ራስን ለመቻል ለሚደረገው ጥረት የጎላ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው አምባሳደር ተፈራ መግለጻቸውን የሚሲዮኑ መረጃ አመላክቷል።

በዚህም ሚሲዮኑ ለኮርፖሬሽኑ አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ በፍጥነት ወደ ስራ የሚገባበትን መንገድ እንደሚመቻች አረጋግጠዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.