Fana: At a Speed of Life!

በዓሉን በአግባቡ ብንጠቀምበት አሰባሰቢ ትርክቶችን ለማጉላት ይጠቅማል- የበዓሉ ታዳሚዎች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓልን በአግባቡ ብንጠቀምበት አሰባሰቢ ትርክቶችን ለማጉላት ይጠቅማል ሲሉ በጅግጅጋ በዓሉን ለመታደም የተገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ገለፁ።
 
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የበአሉ ታዳሚዎች ለዓመታት የተሰበከው መርዛማ አሉታዊ ትርክት ለሰላምና ፀጥታ ችግሩ መንስኤ ናቸው ብለዋል።
 
ታሪክና እውነታችን የሚያስረዳን የተለያየ ቋንቋ ፣ አለባበስና ባህሎች ያሉን በአንድ ጥላ ስር የተሰባሰብን ወንድማማቾች መሆናችንን ነው ሲሉም ተናግረዋል።
 
የኢትዮጵያን እድገት ለማፋጠንና መፃኢ እድሏን ለማስዋብ አሰባሳቢ ትርክቶችን ማጉላት የግድ ይሆናል ሲሉም በአፅንኦት ተናግረዋል።
 
በማርታ ጌታቸው
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.