በድምቀት የተከበረው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በሰላም ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በድምቀት የተከበረው 18ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በሰላም መጠናቀቁን የጅግጅጋ ከተማ ከንቲባ አቶ ዚያድ አብዲ ገለጹ።
በበዓሉ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህን ጨምሮ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የከተማ አስተዳደሮች ከንቲባዎች፣ የብሔር ብሔረሰቦች ተወካዮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
‘ብዝሃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት’ በሚል መሪ ሀሳብ የተከበረው በዓሉ ሀገራዊ አንድነትና ሕብረ ብሔራዊነትን ማጠናከር በሚያስችል መልኩ ተከብሯል።
ከሕዳር 25 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሲከበር የቆየው 18ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ሀገራዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ ሁነቶች ሲከናወኑ ቆይቶ ዛሬ በሰላም ተጠናቋል።
በመላኩ ገድፍ