Fana: At a Speed of Life!

ሁለት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፎቶ በመነሳት ላይ ሳሉ ወንዝ ውስጥ ወድቀው ህይወታቸው አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፎቶ በመነሳት ላይ ሳሉ ወንዝ ውስጥ በመውደቃቸው ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ፡፡

በወላይታ ሶዶ ከተማ ሁምቦ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ ወንዝ ውስጥ ነው አደጋው የተከሰተው፡፡

ሁለቱ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ ዓመት ተማሪዎች ወንዙ ዳርቻ ላይ ፎቶግራፍ በመነሳት ላይ ሳሉ ተንሸራተው ወደ ወንዙ በመግባታቸው የሁለቱም ተማሪዎች ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን መረጃ አመላክቷል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ለአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በጠየቀው ድጋፍ መሰረት የኮሚሽኑ ጠላቂ ዋናተኞች የወጣቶቹን አስከሬን ዛሬ ህዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም አውጥተው አስረክበዋል።

ተማሪዎችና ወጣቶች ፎቶ ግራፍ ለመነሳትና ለመዝናናት በሚል ወንዝ አካባቢ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ መሰል አደጋዎች የሚያጋጥሙ በመሆኑ ወንዝ አካባቢና የመዋኛ ስፍራዎች አካባቢ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ ኮሚሽኑ አሳስቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.