አንበሳ ባንክ በትግራይ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚሆን የ25 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አንበሳ ባንክ በትግራይ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚሆን የ25 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ እንዲደረግ ባደረገው ጥሪ መሰረት ነው ባንኩ ድጋፍ ያደረገው ተብሏል፡፡
ድጋፉን የአንበሳ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ዳንኤል ተኸስተ በመቐለ ተገኝተው ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሥራ ሀላፊዎች አስረክበዋል፡፡
ባንኩ በቀጣይም ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ዳንኤል በመርሐ ግብሩ ወቅት ገልጸዋል፡፡