በአማራ ክልል ከ5 ሺህ በላይ ታጣቂዎች ወደ ማዕከሎች መግባታቸው ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 5 ሺህ 216 ታጣቂዎች ሰላምን መርጠው ወደ ማዕከሎች መግባታቸውን የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡
የቢሮው ኃላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር) በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሰጡት መግለጫ÷ ከሕዝብ የተነሳውን ጥያቄ መሠረት በማድረግ መንግሥት የሰላም ጥሪ ማቅረቡን አስታውሰዋል፡፡
የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና ወጣቶች ታጣቂዎችን በማግባባት ወደ ማዕከል እንዲገቡ እያደረጉ መሆናቸውንም አንስተዋል፡፡
ይህን ተከትሎም በአራቱም ቀጣናዎች 5 ሺህ 216 ታጣቂዎች ሰላምን በመምረጥ ወደ መቀበያ ማዕከላት ገብተዋል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
ለሰላም ሲመጡም መከላከያ ሠራዊት ጥበቃ እያደረገ መሆኑን ያነሱት፥ በቀጣይም በርካታ ታጣቂዎች እንደሚገቡ ይጠበቃል ነው ያሉት።
ለገቡት ታጣቂዎችም አስፈላጊው ጥበቃ እና እንክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑን በመጥቀስም፥ ታጣቂዎችን ወደ ሥልጠና ማዕከል ለማስገባት እየተሠራ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
ክልሉ ዘላቂ ሰላም እንዲኖረው፣ አርሶ አደሮች እንዲያመርቱ፣ በምጣኔ ሀብት ተወዳዳሪ መሆን እንዲቻል ሁሉም ለሰላም ዋጋ እንዲከፍልም ጠይቀዋል።
ታጣቂዎች ጥሪውን በመቀበል ለክልሉ ሰላም መረጋገጥ አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!