Fana: At a Speed of Life!

በጅቡቲ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የተመራው ልዑክ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየምን ጎበኘ

 

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅቡቲ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ድልኤታ መሀመድ ድልኤታ የተመራው የልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየምን ጎብኝቷል፡፡

በፕሬዚዳንቱ የተመራው የልዑካን ቡድን ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ደረጃ የሰው ዘር አመጣጥ ላይ ያሉ ዓለም አቀፋዊ የአንትሮፖሎጂ ግኝቶችን፣ የኢትዮጵያን ሥልጣኔ የሚያሳዩ አርኪዎሎጂዎችንና ታሪካዊ ቅርሶችን ጎብኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ÷ ኢትዮጵያ ቀደምት የሥልጣኔ ምንጭ በመሆኗ በዓለም ደረጃ የተገኙ አርኪዎሎጂዎችና ታሪካዊ ቅርሶችን አስጎብኝተዋቸዋል፡፡

የጅቡቲ ሞክር ቤት ፕሬዚዳንት ድልኤታ መሀመድ ድልኤታ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ተገኝተው ባደረጉት ጉብኝት ደስተኛ መሆናቸውን መናገራቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

እንዲሁም ልዑኩ በአንድነት ፓርክ የሚገኙ የዙፋን ቤትን፣ የአንድነት ፓርክ ቤተ መዛግብትን፣ የአፄ ምኒልክ የግብር አዳራሽን፣ የአንድነት ፓርክ መካነ እንስሳትን እና ክልሎችን የሚወክሉ እልፍኞችን ተመልክተዋል፡፡

የምክር ቤት ፕሬዚዳንቱ በአንድነት ፓርክ የተመለከቷቸው ቅርሶችና ሥራዎች ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካውያንም ኩራት መሆናቸውን በጉብኝቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡

ቡደኑ በነበረው ጉብኝትም የምስራቅ አፍሪካና የኢጋድ የወዳጅነት ቡድን አባላት እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት ዋና ፀሐፊ ምስራቅ መኮንን (ዶ/ር) ተገኝተዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.