ሳዑዲ በህገወጥ መንገድ ወደሀገሯ ገብተው በማቆያ የሚገኙ ዜጎችን በተመለከተ በጋራ መስራት እንደምትፈልግ አስታወቀች
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ድንበር ጥሰው ወደ ሳዑዲ አረቢያ የገቡና በማቆያ የሚገኙ ዜጎችን በተመለከተ በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ የሀገሪቱ አስተዳደር ሚኒስትር ልዑል አብዱልአዚዝ ቢን ሳዑድ ቢን ናይፍ አስታወቁ፡፡
ሚኒስትሩ በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሌንጮ ባቲን በጽ/ቤታቸው አነጋግረዋል፡፡
በውይይቱ ወቅት ልዑል አብዱልአዚዝ ቢን ሳዑድ ቢን ናይፍ፥ ኢትዮጵያ ለሳዑዲ አረቢያ ታሪካዊ ወዳጅ እና ጥብቅ አጋር መሆኗን አንስተዋል፡፡
በሀገራቱ መካከል ካለው የንግድ፣ የትምህርትና ቀጠናዊ ትብብር ባሻገር ሳዑዲ አረቢያ ለኢትዮጵያ ዜጎች የሰጠችውን የስራ ስምሪት እድል በሰፊው እንደምትቀጥልም ነው የተናገሩት፡፡
ሆኖም ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ወደ ሳዑዲ አረቢያ የገቡና በማቆያ የሚገኙ ዜጎች ጉዳይ ላይ በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
አምባሳደር ሌንጮ ባቲ በበኩላቸው፥ በሳዑዲ አረቢያና በኢትዮጵያ መካከል እየተሻሻለ የመጣውን የሁለትዮሽ ግንኙነት አድንቀዋል፡፡
በቀጣይ ከዜጎች ጉዳይ ባለፈ በሌሎች የትብብር መስኮች በጋራ ለመስራት የኢትዮጵያ ፍላጎት እንደሆነ ገልጸዋል።
በቀጣይም በሀገራቱ መካከል ሊኖሩ በሚገባቸው የትብብር መስኮች ዙሪያም መምከራቸውን በሪያድ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!