በጎንደር ተቋርጠው የነበሩ የመንገድ አውታሮች ግንባታን ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ተቋርጠው የነበሩ የመንገድ አውታሮች ግንባታን ለማጠናቀቅ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎንደር አካባቢ ፕሮጀክቶች አስተዳደር ጽህፈት ቤት ገለጸ።
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎንደር አካባቢ ፕሮጀክቶች አስተዳደር ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ ብሩክ አዳነ (ኢ/ር) ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ በጸጥታ ችግርና በተለያዩ ምክንያቶች ተቋርጠው የነበሩ በፕሮጀክት አስተዳደር ጽህፈት ቤቱ ስር የሚገኙ የመንገድ አውታሮችን ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው።
ስራ አስኪያጁ ለረጅም ጊዜ ቅሬታ ሲነሳበት የነበረውን የአዘዞ ጎንደር የአስፓልት መንገድ ስራን ጨምሮ ደባርቅ እና ጃናሞራ ወረዳዎችን ለማገናኘት የሚከናወነው ፕሮጀክት አካል የሆነው የበለስ መካነ ብርሃን የ34 ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታ መጀመሩንም ገልጸዋል።
ከኪሎ ሜትር 69 አንገረብ የሚዘልቀው የ72 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ ስራን ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ የገለጸው በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎንደር አካባቢ ፕሮጀክቶች አስተዳደር ጽህፈት ቤት ፥ ከዳባት አጅሬ የሚገነባውን የ44 ኪሎ ሜትር መንገድ አስፓልት ለማልበስም ስራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኙ አስታውቋል።
በበላይነህ ዘላለም
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!