የወተት ምርት፣ የዶሮና የሥጋ ምርት መጠን በዕቅዱ መሠረት ጥሩ ውጤት አምጥቷል – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 ዓ.ም የወተት ምርት፣ የዶሮ እና የሥጋ ምርት መጠን በዕቅዱ መሠረት ጥሩ ውጤት ማምጣቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የሌማት ትሩፋት የወተት፣ የዶሮ፣ የዕንቁላል፣ የማር፣ የዓሣ እና የሥጋ ምርቶችን ለማሻሻል ሀገራዊ የመንግሥት ፕሮግራም ሆኖ እየተተገበረ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡
በ2015 ዓ.ም የወተት ምርት፣ የዶሮ እና የሥጋ ምርት መጠን በዕቅዱ መሠረት ጥሩ ውጤት አምጥቷል ነው ያሉት።
በያዝነውም ዓመትም የበለጠ ለማሳካት የሁላችንን ያላሰለሰ ጥረት ይሻል ሲሉ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡