Fana: At a Speed of Life!

የፓን አፍሪካ ፓርላማ አባላት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፓን አፍሪካ ፓርላማ የሴቶች አባላት ቡድን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎብኝቷል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ÷ ለአባላቱ ኢመደአ እየሰራቸው የሚገኙ ስራዎችን አስመልክተው ገለጻ አድርገዋል።

አፍሪካውያን የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን በማረጋገጥ ከሳይበር ቅኝ ግዛት እና ከውጭ የቴክኖሎጂ ጥገኝነት በመላቀቅ በምህዳሩ ሉዓላዊነታቸውን ማስከበር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

የፓን አፍሪካ ም/ቤት ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ በበኩላቸው÷ቴክኖሎጂን በማበልፀግና የሀገራችንን ሉዓላዊነት በማረጋገጥ ረገድ አስተዳደሩ እየሰራቸው ያሉ ስራዎች ለሀገር ብሎም ለአፍሪካ የኩራት ምንጭ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የጉብኝቱ ተሳታፊዎች በአፍሪካነታቸው እንዲኮሩ ያደረገ ስራ መሰራቱንም ዶ/ር አሽበር አንስተዋል።

በጉብኝቱ የተሳተፉ የፓን-አፍሪካ ፓርላማ አባላት ባዩት ሀገር በቀል የቴክኖሎጂ ምርትና አገልግሎቶች እንደተደሰቱ መግለጻቸውን የአስተዳደሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

በተለይም ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ታዳጊዎች አቅማቸውን አውጥተው እንዲጠቀሙ በታለንት ማዕከል መታገዛቸው ይበል የሚያሰኝና ለአፍሪካ ሀገራትም እንደ ተሞክሮ የሚወሰድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.