“ብዝኃነትን መኖር” በሚል መሪ ሃሳብ የአብሮነት ቀን ለ14ኛ ጊዜ ሊከበር ነው
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “ብዝኃነትን መኖር” በሚል መሪ ሃሳብ የአብሮነት ቀን ለ14ኛ ጊዜ ሊከበር ነው፡፡
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ወርቅነሽ ብሩ፣ የትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ኮራ ጡሽኔ እና የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት ተወካይ ተስፋዬ ውብሸት ጉዳዩን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል ።
በዚህም የአብሮነት ቀን ሲከበር ብዝሃነትን በሚያጎላ እንዲሁም በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና ፓለቲካዊ ጉዳዮች በአብሮነት የዘለቁ እሴቶችን በሚያንፀባርቅ መልኩ እንደሚሆን ተነስቷል።
ከተለያዩ ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች የተቀናጀ ኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሰራ መሆኑም በመግለጫው ተመላክቷል፡፡
በዚህ መሰረትም የአብሮነት ቀን ከመጪው ሰኞ ጀምሮ በተለያዩ ሁነቶች ተከብሮ ታህሳስ 25 ቀን 100 ሺህ ሰው በሚታደምበት መድረክ ይጠናቀቃል ተብሏል።
በትዕግሰት አስማማው