በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በበጋ መስኖ 81 ሺህ ሄክታር በዘር ተሸፈነ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በበጋ መስኖ ለማልማት ከታቀደው ውስጥ 81 ሺህ ሄክታር በዘር መሸፈኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ኃላፊ ኃይለማርያም ተስፋዬ እንዳሉት÷ በመስኖ የመጀመሪያው ዙር 121 ሺህ ሄክታር ለማልማት እየተሠራ ነው፡፡
ከዚህ ውስጥም 8 ሺህ 778 ሄክታሩ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡
እስካሁንም 2 ሺህ 100 ሄክታር ስንዴን ጨምሮ 81 ሺህ ሄክታር መሬት በዘር ተሸፍኗል ብለዋል፡፡
የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሻሻል ከዚህ በፊት በመስኖ ከአትክልትና ፍራፍሬ በአማካይ በሄክታር የሚገኘውን 150 ኩንታል ወደ 230 ኩንታል ለማሳደግ ግብ መያዙንም አመላክተዋል፡፡
እስከ ጥር ወር መግቢያ ድረስ የመስኖ ልማቱን ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ ለበልግ አዝመራ ዝግጅት እንደሚደረግም አስታውቀዋል፡፡
በበልግ ልማቱም በ702 ሺህ ሄክታር ላይ የአገዳ፣ ብርዕ፣ ጥራጥሬና የቅባት ሰብሎችን ለማልማት ታቅዷል ነው ያሉት፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!