Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል 31 የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል ጥራትና አግባብነት ባልተከተለ መልኩ ከደረጃ በታች ሲያሰለጠኑ በተገኙ 31 የግል የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ላይ እርምጃ መውሰዱን ተገለጸ፡፡

የክልሉ የስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ኃላፊ ሀገረ ጽዮን አበበ፥ ቢሮው ባለፉት ሁለት ዓመታት በክልሉ የሚገኙ የግል የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ብቁ ዜጋን ለማፍራት ያለባቸውን ክፍተት ለመሙላት ድጋፍና ክትትል ሲደረግ መቆየቱን ተናግረዋል

በክልሉ 54 የግል ኮሌጆች መኖራቸውን ጠቅሰው፥ የክትትልና ቁጥጥር ስራ በከፍተኛ ትኩረትና ጥንቃቄ መከናወኑን ነው ያስታወቁት።

በዚህም ተገቢ የስልጠና ሂደት ያላሟሉና ከተቀመጠው ደረጃ በታች ተማሪ ተቀብለው ሲያሰለጥኑ የተገኙ 31 የግል ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ላይ እርምጃ መውሰዱን ገልጸዋል።

በተደረገው ክትትል የተቀመጠውን ጥራትና አግባብነት ባልተከተለ መልኩ እያሰለጠኑ መሆናቸው የተደረሰባቸው 24 ኮሌጆች ከዘርፉ እንዲወጡ የማድረግ እርምጃ መወሰዱንም ነው የተናገሩት።

በኮሌጆቹ ስልጠና ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች ሙሉ ፋይላቸውን እንዲያስረክቡ በማድረግ እንደፍላጎታቸው በመንግስትና በሌሎች ህጋዊ የስልጠና ሂደትን በሚከተሉ ኮሌጆች ስልጠናውን ካቆሙበት እንዲከታተሉ ይደረጋል ብለዋል።

የወቅቱ ገበያ በሚፈልገው መሰረት በፈጠራ፣ በዕውቀትና በክህሎት የበቃ ዜጋን ለማፍራት የሚያስችሉ የስልጠና ተቋማትን በተቀመጠው ደረጃ መሰረት የማደራጀት ስራ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ዘንድሮም የተማሪ ቅበላ መጀመሩን አንስተው፤ ገበያውን ያላገናዘቡ ተቋማት ከማሰልጠን እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.