Fana: At a Speed of Life!

እንደ ሀገር ገዥ ትርክትን በማስረጽ ብሔራዊነትን ማጎልበት እንደሚገባ ተመለከተ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራዊ ገዥ ትርክትን በማስረጽ ብሔራዊነትን ማጎልበት ለብልጽግና ጉዞ ወሳኝ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ዋና ተጠሪ ዓለማየሁ ባውዲ ገለጹ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት የተከለሰ ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር መክሯል።

አቶ ዓለማየሁ ባውዲ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ኢትዮጵያን ከፋፋይ ከሆነ ትርክት በማላቀቅ ኅብረ-ብሔራዊነትን በማጉላት ረገድ የሚዲያ ባለሙያዎች እንዲያደርጉ ተይቀዋል፡፡

የሀገራዊ ምክክር ሥራው ስኬታማ እንዲሆንም በሕዝቦች መካከል ተግባቦት ሊፈጥሩ የሚችሉ ሥራዎች ሊሠሩ እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡

የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ሰናይት ሰለሞን በበኩላቸው÷ በክልሉ የሕዝቦችን አንድነት የሚያጠናክሩ የሚዲያ ሥራዎች ይሠራሉ ብለዋል።

የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎችም የክልሉን ሕዝብ ልማትና አንድነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ በትኩረት እንዲሠሩ አሳስበዋል፡፡

በጥላሁን ሁሴን

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.