Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል 487 ቢሊየን ብር ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል 487 ቢሊየን ብር ያስመዘገቡ 1 ሺህ 12 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መውሰዳቸውን የክልሉ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ገለጸ።

የቢሮው ሃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት÷ በክልሉ በተለያዩ ዘርፎች የኢንቨስመንት ፈቃድ የወሰዱ ባለሃብቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል፡፡

ባለሃብቱ ከሃይል አቅርቦት እና ከመሬት ጋር ተያይዞ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች ቢሮው ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመነጋገር እንደሚፈታ አንስተዋል፡፡

አልሚ ባለሃብቶች ወደ ስራ ሲገቡ 117 ሺህ 276 ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል ይፈጥራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመላክቷል፡፡

በእሸቱ ወ/ሚካኤል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.